የትግራይ ነጋዴዎች የተበደሩት ዕዳ ከእጥፍ በላይ ኣድጓል

የትግራይ ክልል ነጋዴዎች ከጦርነቱ በፊት ተበድረውት የነበረው 32 ቢሊዮን ብር አሁን ከነወለዱ ወደ 80 ቢሊዮን ብር አድጓል ተባለ፡፡

ይህን ያለው ትግራይ ክልል ንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ነው፡፡

የትግራይ ክልል ንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዘዳንት አቶ በሪሁን ሃፍቱ የትግራይ ክልል ነጋዴዎች ከጦርነቱ በፊት ከባንክ ወስደውት ነበረው የባንክ እዳ በአምስት አመት ወስጥ ከ32 ቢሊዮን ብር አሁን ከነወለዱ ወደ 80 ቢሊዮን ብር ደርሷል ብለዋል፡፡

አቶ በሪሁን በክልሉ ተከስቶ የነበረው ጦርነት ብዙ ሀብት አውድሟል የንግድ እና ኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን አጥፍቷል፣ ቀሪዎችንም ከንግድ እንቅስቃሴ ውጭ አድርጎ የገበያ ትስስራቸውን እንዲያጡ አድርጓል ሲሉ አስረድተዋል፡፡

እነዚህ የወደሙ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች የጠፉት ደግሞ የባንክ ብድር ይዘው ነው ሲሉ አቶ በሪሁን ተናግረዋል፡፡

የባንክ እዳ ይዘው የወደሙ የንግድ ተቋማትን ወደ መደበኛ ሥርዓት ለመመለስ ከባድ ነው ፤ ምክንያቱም ባለሀብቱ ፈልጎ ባላመጣው ጦርነት ተዳክሟል ብለዋል አቶ በሪሁን፡፡

በክልሉ ያሉ ባለሀብቶች ንብረታቸው መውደሙ እና ሀብታቸው መጥፋቱ ሳያንስ እዳቸውን ከነወለዱ እና ከነቅጣቱ እንዲከፍሉ እየተገደዱ ነው፤ ይህም አግባባብ አደለም ምክኒያቱም በለሃብቶች ጦርነቱን ፈልገውት አይደለም ያመጡት ሲሉ አቶ በሪሁን ተናግረዋል፡፡

የትግራይ ክልል ንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዘዳንት አቶ በሪሁን ሃፍቱ የወደሙ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ተቋማት ተመልስው ወደስራ የሚገቡበት ሁኔታ ሳይፈጠር ባለሃብቶች ባልሰሩበት የተበደሩትን እዳ ከነወለዱ እንዲከፍሉ መደረጉ ተገቢ አይደለም መከፈል ግዴታም ከሆነም ደግሞ ቢያንስ እየሰሩ እንዲከፍሉ ልዩ ማበረታቻ ያሰፈልጋቸዋል ብለዋል፡፡

ፕሬዘዳንቱ የወደሙትን በአዲስ ለመተካት የተዳከሙትን ደግሞ ለማነቃቃት ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ያን ማድረግ የሚቻል ከሆነ ነጋዴው ነግዶ አትርፎ አዲስ ግብር ከፋይ ብቻ ሳይሆን ከዚህ በፊት የነበረበትን እዳም የመክፈል አቅም ይኖረዋል ሲሉ አስረድተዋል፡፡

አሁን ያለብን ትልቁ ችግር ተጨማሪ ድጋፍ አለማግኘት ነው ያሉት አቶ በሪሁን ባንኮች ተጨማሪ ብድር ለመስጠትም እየተቸገሩ ነው ያሉት ብለዋል፡፡

ባለሃብቶች ከጦርነቱ በፊት የተበደሩት እዳ ወለዱም ከዛሬ ነገ እየጨመረ ነው ያለው ፤ አይደለም ሰርቶ ማትረፍ ይቅርና ስራ በቆመበት እና ንብረት በወደመበት ወቅትም ወለዱ እየታሰበ ነው ያ ወለድ ደግሞ የወለድ ወለድ ቅጣት እየታሰበበት ነው ብለዋል ፕሬዘዳንቱ
የትግራይ ክልል ንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዘዳንት አቶ በሪሁን ሃፍቱ ያለው ችግር የተለየ የብደር ጥቅል ካልተዘየደለት አሁን ባለው አሰራር የሚፈታ እንዳልሆነ ነግረውናል፡፡

ምክንያቱም የወደመው ንብረት በቢሊዮን የሚገመት ነው ያሉት አቶ በሪሁን በዚህ ላይ ደግሞ የኢኮኖሚው ማሻሽያ ሲጨመር ችግሩን የከፋ አድርጎታል ብለዋል፡፡
ጦርነቱ ከቆመ ወዲህ ባለፉት ሁለት አመታት ለክልሉ ባለሃብቶች የቀረበው ብድር 2 ቢሊዮን ብር የማይሞላ እንደሆነ ተነግሯል፡፡ ይህም ከችግሩ ስፋት ጋር አብሮ የሚሄድ አይደለም ተብሏል፡፡

በቅረቡ ከብሄራዊ ባንክ ጋር ወይይት ማድረጉን የተናገው ምክር ቤቱ በዚህም ነጋዴዎች በሐራጅ ለመሸጥ ጊዜውን ለአንድ አመት እንዲራዝም ተደርጓል ግን ይህ በቂ አይደለም ብሏል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *